የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፥ “በንጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእናንተም እኛ እንቀድማለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳዊትም ከእናንተ እኛ እንቀርባለን፤ ስለምን ናቃችሁን? ንጉሡንስ እንመልሰው ዘንድ ከእናንተ የእኛ ቃል አይቀድምምን?” አሏቸው። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ።
1 ነገሥት 11:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮርብዓምንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከሰሎሞን እጅ መንግሥቱን እለያታለሁ፤ ዐሥሩንም ነገዶች እሰጥሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮርብዓምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቍራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ መንግሥቱን ከሰሎሞን እጅ እቀድዳለሁ፤ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጣለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘መንግሥትን ከሰሎሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ “ዐሥሩን ቊራጭ ለራስህ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘መንግሥትን ከሰሎሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮርብዓምንም አለው “ዐሥር ቁራጭ ውሰድ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ‘እነሆ፥ ከሰሎሞን እጅ መንግሥቱን እቀድዳለሁ፤ ዐሥሩንም ነገዶች እሰጥሃለሁ፤ |
የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፥ “በንጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእናንተም እኛ እንቀድማለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳዊትም ከእናንተ እኛ እንቀርባለን፤ ስለምን ናቃችሁን? ንጉሡንስ እንመልሰው ዘንድ ከእናንተ የእኛ ቃል አይቀድምምን?” አሏቸው። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ።
እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አፍ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
ኢዮርብዓምም ሚስቱ ሐኖንን፥ “ተነሺ፥ ራስሽን ለውጪ የኢዮርብዓምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለዚህም ሕፃን ከደዌው ይድን እንደሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደምነግሥ የነገረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።
ከዳዊትም ቤት፤ መንግሥቱን ከፍዬ ሰጥቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍጹም ልቡ እንደ ተከተለኝ፥ በፊቴም ቅን ነገር ብቻ እንዳደረገ፥ ትእዛዜንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪያዬ እንደ ዳዊት አልሆንህም።
እስራኤልም ከዳዊት ቤት ተለዩ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።
እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም የተናገረውን ቃሉን እንዲያጸና ለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
ሳሙኤልም፥ “እግዚአብሔር ከእስራኤል መንግሥትህን ዛሬ ከእጅህ ቀደዳት፤ ከአንተም ለሚሻል ለባልንጀራህ አሳልፎ ሰጣት፤