ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ከበሮንና መሰንቆንም መቱ፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።
1 ነገሥት 1:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከት ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ በከተማ የምሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዶንያስና የተጠሩት እንግዶች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ፣ ይህንኑ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከቱን ድምፅ ሲሰማ፣ “ይህ በከተማዪቱ ውስጥ የሚሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፥ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምፅ በሰማ ጊዜ፦ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምፅ ምንድነው?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዶንያስና የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ የሁካታ ድምፅ ሰሙ፤ ኢዮአብም የእምቢልታ ድምፅ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማው ውስጥ የሚሰማው የሁካታ ድምፅ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምጽ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምጽ ምንድር ነው?” አለ። |
ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ከበሮንና መሰንቆንም መቱ፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።
እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መልካምም ታወራልናለህና ግባ” አለው።
ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ!” እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው
ሊገድሉትም ፈልገው ብዙ ደበደቡት፤ ወዲያውም ኢየሩሳሌም በመላዋ እንደ ታወከች የሚገልጥ መልእክት ወደ ሻለቃው ደረሰለት።