1 ዮሐንስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውን፣ የሰማነውን፣ በዐይኖቻችን ያየነውን፣ የተመለከትነውንና እጆቻችን የዳሰሱትን እንናገራለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመጀመሪያው የነበረውን፥ የሰማነውን፥ በዐይኖቻችንም ያየነውን፥ የተመለከትነውንና እጆቻችንም የዳሰሱትን፥ ስለ ሕይወት ቃል እንናገራለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፤ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነው፥ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ |
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
እጄንና እግሬን እዩ፤ ዳስሱኝም፤ እኔ እንደ ሆንሁም ዕወቁ፤ በእኔ እንደምታዩት ለምትሐት አጥንትና ሥጋ የለውምና።”
ከዚህም በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆችን እይ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው።
ሕማማትን ከተቀበለ በኋላ ብዙ ተአምራት በማሳየት አርባ ቀን ሙሉ እየተገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸውና እያስተማራቸው ሕያው ሆኖ ራሱንገለጠላቸው።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበረና የሰሙትም ለእኛ አጸኑት።
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።