ጳውሎስም ከእርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚያም ሀገር ስለ አሉት አይሁድ ወስዶ ገረዘው፤ አባቱ አረማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበርና።
1 ቆሮንቶስ 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድን እጠቅማቸው ዘንድ ለአይሁድ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁላቸው፤ ከኦሪት በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦሪት በታች ሳልሆን ከኦሪት በታች ላሉት ከኦሪት በታች እንዳለ ሰው ሆንሁላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድን እመልስ ዘንድ ከአይሁድ ጋራ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፣ ከሕግ በታች ያሉትን እመልስ ዘንድ ከሕግ በታች እንዳሉት ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድንም ለመጥቀም ስል ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን መጥቀም እንድችል፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአይሁድ ጋር ስሆን አይሁድን ለማዳን እንደ አይሁዳዊ ሆንኩ፤ እኔ ከሕግ በታች ባልሆንም እንኳ ከሕግ በታች ያሉትን ለማዳን ስል ከሕግ በታች እንዳሉት ሰዎች ሆንኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤ |
ጳውሎስም ከእርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚያም ሀገር ስለ አሉት አይሁድ ወስዶ ገረዘው፤ አባቱ አረማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበርና።
ጳውሎስም እንደ ገና በወንድሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጠ፤ በሰላምም ሸኙትና ወደ ሶርያ በባሕር ተጓዘ፤ ጵርስቅላና አቂላም አብረውት ነበሩ፤ ስእለትም ነበረበትና በክንክራኦስ ራሱን ተላጨ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።