1 ቆሮንቶስ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የምሥጢሩ መጋቢዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እንዲህ ያስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢራት መጋቢዎች ይቁጠረን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን የክርስቶስ አገልጋዮች እንደ ሆንን የእግዚአብሔርንም ምሥጢር የመግለጥ ኀላፊነት የተሰጠን ባለ ዐደራዎች እንደ ሆንን አድርጎ ሊቈጥረን ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቍጠረን። |
እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነዚያ ግን አይተው እንዳያዩ፥ ሰምተውም እንዳይሰሙ፥ እንዳያስተውሉም በምሳሌ ነው።
ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና።
ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ።
ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔር ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።
እንግዲህ ጳውሎስ ምንድን ነው? አጵሎስስ ምንድን ነው? እነርሱስ በቃላቸው የአመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ሰጠው ነው።
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ቢሆኑም እኔም እንደ ሰነፍ ለራሴ እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ እጅግም ደከምሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገረፍሁ፤ ብዙ ጊዜም ታሰርሁ፤ ብዙ ጊዜም ለሞት ተዘጋጀሁ።
ልመካ ብሻም አላዋቂ አይደለሁም፤ እውነቱን እናገራለሁና፤ ነገር ግን ስላዩኝና ስለ ሰሙኝ እንደምበልጥ አድርገው እንዳይጠራጠሩኝ ትቸዋለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ እንደ ሆነ እንሰብካለን እንጂ ራሳችንን የምንሰብክ አይደለም፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም ብለን ራሳችንን ለእናንተ አስገዛን።
ነገር ግን በሁሉ ራሳችንን አቅንተን፥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንሁን፤ በብዙ ትዕግሥትና በመከራ፥ በችግርና በጭንቀት ሁሉ፥
ይኸውም ልቡናቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትምህርታቸውም በማወቅ፥ በፍቅርና ፍጹምነት ባለው ባለጸግነት፥ በጥበብና በሃይማኖት፥ ስለ ክርስቶስም የሆነውን የእግዚአብሔርን ምክር በማወቅ ይጸና ዘንድ ነው።
ስለ እርሱ የታሰርሁለትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንድንናገር፥ እግዚአብሔር የቃሉን በር ይከፍትልን ዘንድ ለእኛም ደግሞ ጸልዩልን፤ ለምኑልንም፤
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
ኤጲስቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥
ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤