ፈራ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህችም የሰማይ ደጅ ናት።”
1 ቆሮንቶስ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚያፈርሰውን ግን እርሱን ደግሞ እግዚአብሔር ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እንግዲያስ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አታርክሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፤ ያም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይኼውም እናንተ ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ሰው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይህም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ። |
ፈራ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህችም የሰማይ ደጅ ናት።”
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቤት ስለ ወደድሁ፥ ለመቅደሱ ከሰበሰብሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና እነሆ፥ ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
በተራራው ራስ ላይ ያለውን ቤቱንና የቤቱን ሥርዐት ሣል፤ የዙሪያውም ዳርቻ ሁሉ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። እነሆ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።”
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም።
“እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ድንኳኔን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው አንጹአቸው።
መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የቅዱሳኔንም ስም ያጐስቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሶአልና ከማኅበሩ መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ በሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ነው።
እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንፈስም በእናንተ ላይ አድሮ እንደሚኖር አታውቁምን?
ራሳችሁን አታስቱ፤ ከመካከላችሁ በዚህ ዓለም ጥበበኛ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላዋቂ ያድርግ።