La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍቅር ሁሉን ይታገሣል፤ ሁሉን ያምናል፤ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉ ነገር ይጸናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍቅር ያለው ሰው ሁሉን ይችላል፤ በሁሉም ላይ እምነቱን ይጥላል፤ በሁሉም ላይ ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉ ነገር ይጸናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 13:7
29 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።


እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።


ቍጣ ጥልን ያነሣሣል። ፍቅር ግን የማይጣሉትን ሁሉ ይሸፍናቸዋል።


በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


ኢየሱስም “ቢቻልህ ትላለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፤” አለው።


የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።


የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ ማድ​ረግ ተስፋ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንማ እን​ዴት ተስፋ ያደ​ር​ጋል? እን​ዴ​ትስ ይጠ​ብ​ቃል?


ፍቅር ያስ​ታ​ግ​ሣል፤ ፍቅር ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ናል፤ ፍቅር አያ​ቀ​ና​ናም፤ ፍቅር አያ​ስ​መ​ካም፤ ፍቅር ልቡ​ናን አያ​ስ​ታ​ብ​ይም።


በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።


ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን ሸክም ይሸ​ከም፤ በዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሕግ ትፈ​ጽ​ማ​ላ​ችሁ።


“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፦ እኔ ብቻ​ዬን ልሸ​ከ​ማ​ችሁ አል​ች​ልም፤


በሜዳ ባገ​ኛት ጊዜ የታ​ጨ​ችው ልጃ​ገ​ረድ ጮኻ​ለ​ችና፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ትም አል​ነ​በ​ረ​ምና።


ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።


የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፥ ለማስተማርም የሚበቃ፥ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።


ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።


አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፤ አገልግሎትህን ፈጽም።


አሁ​ንም ተግ​ዳ​ሮ​ቱን ተሸ​ክ​መን፥ ወደ እርሱ ወደ ከተ​ማው ውጭ እን​ውጣ።


በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።


ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኀጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።