የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ከክፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፥ “እንግዲህ በቃህ፤ እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበረ።
1 ቆሮንቶስ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጐራጐሩበት፥ በመቅሠፍትም እንደጠፉ አናንጐራጕር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳጕረመረሙና በአጥፊው እንደ ጠፉ፣ አታጕረምርሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳጉረመረሙና በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታጉረምርሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳጒረመረሙና በቀሳፊው መልአክ እንደ ጠፉ እናንተም አታጒረምርሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጕኦርጕሩ። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ከክፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፥ “እንግዲህ በቃህ፤ እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበረ።
እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ከመቅሠፍቱ ይቅር አለ፤ የሚያጠፋውንም መልአክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ በአየ ጊዜ እግዚአብሔር በሩን ያልፋል፤ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተወውም።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከምንሞት በግብፅ ምድር ሳለን ብንሞት በተሻለን ነበር።
ስለዚያችም ምድር ክፉን ነገር ተናገሩ፤ ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ፤ ምድሪቱ ግን መልካም ነበረች።
ስለዚህም አንተና ማኅበርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማንነው?”
በነጋውም የእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።”
እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።”
እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።