1 ዜና መዋዕል 4:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሰዔ ልጆች ፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚሁ ዐምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኰረብታማ አገር ወረሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስምዖን ዘሮች አምስት መቶ የሚሆኑት ወደ ኤዶም ተራራ ሄዱ፤ እነርሱም ይመሩ የነበሩት በዩሽዒ ልጆች በፐላጥያ፥ በነዓርያ፥ በረፋያና በዑዚኤል ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው።