La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃል፤ ታላ​ቅም ሰልፍ አድ​ር​ገ​ሃል፤ በፊ​ቴም በም​ድር ላይ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ለስሜ ቤት አት​ሠ​ራም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤ ‘አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ብዙ ጦርነትም አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለ ሆነ፣ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ውግያ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ብዙ ሰው ገድለሃል፤ በብዙ ጦርነቶችም ላይ ውጊያ አድርገሃል፤ ብዙ ደም በማፍሰስህም ቤተ መቅደስ እንድትሠራ አልፈቅድልህም’ ብሎኛል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ ‘እጅግ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 22:8
9 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ በኋላ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐይን ይመ​ለ​ከ​ት​ሃል።


ንጉ​ሡም የለ​ዘቡ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንና ለቤ​ቱም መሠ​ረት ያል​ተ​ጠ​ረ​በ​ውን ድን​ጋይ ያመጡ ዘንድ አዘዘ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ በዙ​ሪ​ያው ስለ ነበረ ጦር​ነት አባቴ ዳዊት ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት መሥ​ራት እን​ዳ​ል​ቻለ አንተ ታው​ቃ​ለህ።


ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል እንጂ ቤት የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን፦ የሰ​ልፍ ሰው ነህና፥ ብዙ ደምም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ስሜ የሚ​ጠ​ራ​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራም ብሎ​ኛል።


ልብ​ስ​ንም፥ ከቁ​ር​በ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ሁሉ፥ ከፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የተ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ንጹሕ አድ​ርጉ።”


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ልብ​ሳ​ች​ሁን እጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።”