ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞትብኝ ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች።
1 ዜና መዋዕል 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም በአጠቃላይ ዐምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ የልጁ ሚስት ከነበረችው ከትዕማር ፋሬስና ዛራሕ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የይሁዳ ልጆች በድምሩ አምስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ። |
ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞትብኝ ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች።
ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ፥ የሰፋጥያስ ልጅ፥ የሰማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ አታያ፤