La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 16:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 16:34
13 Referencias Cruzadas  

በም​ድር ሊፈ​ርድ ይመ​ጣ​ልና፥ የዱር ዛፎች በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ኤማ​ን​ንና ኤዶ​ታ​ምን፥ በስ​ማ​ቸው የተ​ጻ​ፉ​ትን ተመ​ር​ጠው የቀ​ሩ​ትን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አቆመ።


ከሕ​ዝ​ቡም ጋር ተማ​ክሮ በሠ​ራ​ዊቱ ፊት የሚ​ሄ​ዱ​ትን፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ሉ​ት​ንም፥ በቅ​ድ​ስና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ም​ሩ​ትን መዘ​ም​ራን አቆመ።


መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ እርስ በር​ሳ​ቸው ያስ​ተ​ዛ​ዝሉ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በሩ በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ።


ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ውር የሚ​ያ​ማን እር​ሱን አሳ​ደ​ድሁ፤ በዐ​ይኑ ትዕ​ቢ​ተኛ የሆ​ነ​ውና ልቡ የሚ​ሳ​ሳው ከእኔ ጋር አይ​ተ​ባ​በ​ርም።


ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።


ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።


በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ንጹ​ሓን የሆኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።