La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልንም አምላክ የጌታን ታቦት ለማምጣት ካህናቱና ሌዋውያኑ ተቀደሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው ይወስዱ ዘንድ ካህናትና ሌዋውያን ራሳቸውን አነጹ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህናቱና ሌዋውያኑ ተቀደሱ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 15:14
8 Referencias Cruzadas  

“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።


በመ​ጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ ሙሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ አዘ​ዛ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በት​ከ​ሻ​ቸው ላይ በመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ ተሸ​ከሙ። መባ​እና ቍር​ባ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰብ​ስ​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።


ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


ከመ​ቅ​ደ​ስም ከወጡ በኋላ በዚያ የነ​በ​ሩት ካህ​ናት ሁሉ ተቀ​ድ​ሰው ነበር፤ በሰ​ሞ​ና​ቸ​ውም አል​ተ​ከ​ፈ​ሉም ነበር።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።