1 ዜና መዋዕል 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁላት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ስለ ሆናችሁ፣ እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ ከዚያም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የጌታን ታቦት እንድታመጡ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያኑንም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እናንተ ለሌዋውያን ጐሣዎች መሪዎች ናችሁ፤ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት እኔ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ተሸክማችሁ ታመጡ ዘንድ ራሳችሁንና ሌዋውያን ወገኖቻችሁን ሁሉ ቀድሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊትም በተከለላት ድንኳን ውስጥ አኖሩአት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።
ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ሁሉ ተናገረ።
ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን ታቦት ከቂርያትይዓሪም አወጣት። ለእርሷ በኢየሩሳሌም ድንኳን አዘጋጅቶላት ነበርና።
በሁለተኛውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ተዘጋጁ ነጹም። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
የፋሲካውንም በግ እረዱ፤ እናንተም ተቀደሱ፥ እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ የተናገረውን ቃል ታደርጉ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። “አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ” አልሁ።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
የእስራኤልም ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋውያን እንደ ሳቱ ላልሳቱት፥ ሥርዐቴን ለጠበቁት፥ ከሳዶቅ ልጆች ወገን ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል።