1 ዜና መዋዕል 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አምላኩ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መቱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማድረግ ፍልስጥኤማውያንን ከገባዖን እስከ ጌዜር ድል አድርጎ አባረራቸው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መቱት። |
በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው።
ከዚህም በኋላ በጋዜር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት እንደ ገና ሆነ፤ ያንጊዜም ኡሳታዊው ሴቦቃይ ከኀያላን ወገን የነበረውን ሲፋይን ገድሎ ጣለው።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ደግሞም ጋዜርንና መሰማሪያዋን፤
እግዚአብሔርም በኃጥኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፤ በገባዖን ሸለቆም ይኖራል፤ ሥራውን ማለት መራራ ሥራውን በቍጣ ይሠራል፤ ቍጣውም ድንቅን ያደርጋል፤ መርዙም ልዩ ነው።
በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።