Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሊመታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይወ​ጣ​ልና በዚ​ያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያውኑ ለጦርነት ውጣ፤ ይህም የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቷል ማለት ነውና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሾላውም ዛፍ አናት የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ውግያ ውጣ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔ ፊት ፊትህ ሄጄ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ድል ስለምመታ በዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ አደጋ ጣል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 14:15
16 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በኋ​ላ​ቸው ዞረህ በሾ​ላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠ​ማ​ቸው እንጂ አት​ውጣ።


እነሆ፥ በላዩ መን​ፈ​ስን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ በሉት።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሶ​ር​ያ​ው​ያን የሰ​ረ​ገላ ድምፅ፥ የፈ​ረስ ድም​ፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰ​ምቶአ​ቸ​ዋ​ልና፥ እርስ በር​ሳ​ቸው “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ይከ​ቡን ዘንድ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ነገ​ሥት ቀጥሮ አም​ጥ​ቶ​ብ​ናል” ይባ​ባሉ ነበር።


ዳዊ​ትም እንደ ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አት​ውጣ፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም አት​ከ​ተ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከኋ​ላ​ቸው ዙረህ ቅረ​ባ​ቸው።


ዳዊ​ትም አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ።


በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤


ድን​ገ​ትም እንደ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ከሰ​ማይ ድምፅ መጣ፤ የነ​በ​ሩ​በ​ት​ንም ቤት ሞላው።


ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


ዲቦ​ራም ባር​ቅን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይሄ​ዳል” አለ​ችው። ባር​ቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ከታ​ቦር ተራራ ወረደ።


ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos