ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው።
1 ዜና መዋዕል 11:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይፉንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ በአንድ ጊዜ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች የበላይ አለቃ ነበር፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎችን ገድሎ ስለ ነበር እንደ ሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች ታዋቂ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ። |
ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው።
በዚያም ሦስቱ የሦርህያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ፥ አሣሄልም ነበሩ፤ የአሣሄልም እግሮቹ ፈጣኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳቋም ሯጭ ነበረ።
ዳዊትም አቢሳን፥ “አሁን አቤሴሎም ከአደረገብን ይልቅ የከፋ የሚያደርግብን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዐይናችን እንዳይሰወር፥ አንተ የጌታህን ብላቴኖች ወስደህ አሳድደው” አለው።
የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ይገድሉት ዘንድ ይጠባበቁ ነበር።
“ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይገባኝም፤ ሰውነታቸውንም ለሞት አሳልፈው አምጥተውታልና የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን?” አለ። ስለዚህም ዳዊት ይጠጣው ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው።
በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፥ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም።
ዳዊትም ኬጤያዊዉን አቤሜሌክንና የሶርህያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እገባለሁ” አለ።