Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች የበላይ አለቃ ነበር፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎችን ገድሎ ስለ ነበር እንደ ሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች ታዋቂ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይ​ፉ​ንም በሦ​ስት መቶ ላይ አን​ሥቶ በአ​ንድ ጊዜ ገደ​ላ​ቸው፤ በሦ​ስ​ቱም መካ​ከል ስሙ የተ​ጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 11:20
10 Referencias Cruzadas  

ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፥ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳይ፥ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሠራዊቱ፥ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ እወጣለሁ” አላቸው።


ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብ፥ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ፤


ዳዊትም አቢሳን፥ “ከአቤሴሎም ይልቅ አሁን የቢክሪ ልጅ ሼባዕ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስብን ስለሆነ የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው፤ ያለዚያ የተመሸገ ከተማ አግኝቶ ያመልጠናል” አለው።


የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።


አበኔር ገባዖን ላይ በተደረገው ጦርነት የኢዮአብንና የአቢሳን ወንድም አሣሄልን ገድሎት ስለ ነበር፥ እነርሱም አበኔርን ገደሉት።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “ይህን እንዳደርግ አምላኬ አይፈቅድልኝም፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው አምጥተውታል።” ስለዚህም ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።


በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፥ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ ደረጃ አልደረሰም ነበር።


እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች፤ አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ናቸው፤ ሦስቱ ነበሩ።


ዳዊትም ሒታዊውን አቢሜሌክንና የጸሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ሰፈር አብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፥ “እኔ አብሬህ እወርዳለሁ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos