ሩት 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በሞዓብ ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘና እህል እንደ ሰጣቸው በሰማች ጊዜ፣ ሁለቱን ምራቶቿን ይዛ ወደ አገሯ ለመመለስ ከዚያ ተነሣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ጌታም ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እህልም እንደሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚ በሞአብ አገር ሳለች፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት እንዳደረገላቸውና ብዙ መከር እንደ ሰጣቸው ሰማች፤ ስለዚህ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከሞአብ ወደ እስራኤል ለመመለስ ተነሣች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። |
ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ
ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይሥሐቅ በፊቱ የተመላለሱት እግዚአብሔር፣ ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣
“ሂድና የእስራኤልን አለቆች ሰብስበህ፣ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም፣ የይሥሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፤ ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብጽ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ።
ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰባው ዓመት የባቢሎን ቈይታችሁ በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ ልመልሳችሁ የገባሁላችሁን መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።
ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤ እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ። በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋል፤ ምርኳቸውንም ይመልስላቸዋል።
ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ።