15 እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤ ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።
15 ስንቆቿን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
15 ለጽዮን ምግብዋን አበዛለሁ፤ ድኾችዋንም እስከሚጠግቡ አበላቸዋለሁ።
በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።
የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፤ ሀብታሞችን ግን ባዷቸውን ሰድዷቸዋል፤
ባትሰሙ፣ ልባችሁንም ስሜን ለማክበር ባታዘጋጁ፣ ርግማን እሰድድባችኋለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ መርገም እለውጠዋለሁ፤ ልታከብሩኝ ልባችሁን አላዘጋጃችሁምና ረግሜዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለ ሮጣችሁ ነው፤
ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”
ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤ ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤” ይላል እግዚአብሔር።
ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።
እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቷልና፤ የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቧል።
በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።
በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤ በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ።
ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!
ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፣ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፣ አንተንም አምላክህ እግዚአብሔር በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።
አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ፤ በረከቱም በምትበላውና በምትጠጣው ላይ ይሆናል፤ በሽታንም ከአንተ ዘንድ አርቃለሁ።