መዝሙር 81:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሉ ለሙሉ ግብጽን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣ ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት። በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው። ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤ በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። |
“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
‘ግብጻውያንን በቀሠፈ ጊዜ፣ በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን ቤት ዐልፎ በመሄድ ቤታችንን ላተረፈ፣ ለእግዚአብሔር የፋሲካ መሥዋዕት ነው’ ብላችሁ ንገሯቸው።” ከዚያም ሕዝቡ አጐነበሱ፤ ሰገዱም።
እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኵር ልጅ ጀምሮ፣ በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እስካለው እስረኛ የበኵር ልጅ ድረስ ያለውንና የእንስሳቱን በኵሮች ሁሉ ቀሠፋቸው።
የእስራኤል ቤት ሆይ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከሩቅ ሕዝብን አመጣባችኋለሁ፤ ጥንታዊና ብርቱ፣ ቋንቋውን የማታውቁት፣ ንግግሩንም የማትረዱት ሕዝብ ነው።