La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 61:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ለስምህ ዘወትር ውዳሴ አቀርባለሁ፤ ስእለቴንም በየጊዜው እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፥ ይጠብቁት ዘንድ ቸርነትንና እውነትን አዘጋጅለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለአንተ የተሳልኩትን በየቀኑ በማቅረብ ዘወትር የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ታመኑ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም በፊቱ አፍ​ስሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ታ​ችን ነው።

Ver Capítulo



መዝሙር 61:8
10 Referencias Cruzadas  

የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋራ እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁንም ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ በጎነትና ታማኝነትም ከአንተ ጋራ ይሁን” አለው።


በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።


እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።


ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከብቦኛልና፤ የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዝቷል፤ ልቤም ከድቶኛል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ ለአንተ ስእለት ይፈጸማል።


አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።


እኛ ሕዝብህ፣ የማሰማሪያህ በጎችህ፣ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም፣ ውለታህን እንናገራለን።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤