መዝሙር 56:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤ በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፥ ሁልጊዜም ተዋጊ አስጨንቆኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ያጠቁኛል፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ የሚያሳድዱኝ ብዙዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ልዑል እግዚአብሔር፥ ወደሚረዳኝ እግዚአብሔር እጮኻለሁ። |
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ።