የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋራ እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁንም ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ በጎነትና ታማኝነትም ከአንተ ጋራ ይሁን” አለው።
መዝሙር 43:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፤ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፥ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥ ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥ ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለሃቸዋልና። |
የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋራ እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁንም ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ በጎነትና ታማኝነትም ከአንተ ጋራ ይሁን” አለው።
ከዚያም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማዪቱ ይዘህ ተመለስ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ እርሱ እኔንም መልሶ ታቦቱንና ማደሪያውን እንደ ገና ለማየት ያበቃኛል፤
ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።
ነፍሴ በአንበሶች ተከብባለች፤ በሚዘነጣጥሉ አራዊት መካከል ወድቄአለሁ፤ እነዚህም፣ ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፣ ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሰዎች ናቸው።