መዝሙር 148:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳትና በረዶ፥ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤ |
ስለዚህ ሙሴ በግብጽ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት በሙሉ በምድሪቱ ላይ የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ በማግስቱም ነፋሱ አንበጣዎችን አመጣ።
ከዚያም እግዚአብሔር ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው፤ ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባሕር ከተታቸው፤ በግብጽ ምድር በየትኛውም ቦታ አንድም አንበጣ አልቀረም።
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን በሙሉ ብርቱ የምሥራቅ ነፋስ አስነሥቶ ባሕሩን ወደ ኋላ በማሸሽ ደረቅ ምድር አደረገው፤ ውሃውም ተከፈለ።
ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
መርከበኞቹ ሁሉ ፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱም ክብደት እንዲቀልል፣ በውስጧ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕሩ ጣሉት። ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ፤ በከባድም እንቅልፍ ላይ ነበር።
ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።
በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ ዐምስት ኪሎ ግራም የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ።