ዘኍል 5:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህኑ ሴትዮዋን ያመጣትና በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ያደርጋታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካህኑም ያቀርባታል በጌታም ፊት ያቆማታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑ ሴትዮዋን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ካህኑም ያቀርባታል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያቆማታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ያቀርባታል በእግዚአብሔርም ፊት ያቆማታል፤ |
“ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከላሞች መንጋ መካከል የሚቀርብ ከሆነ፣ ነቀፋ የሌለበትን ተባዕቱን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያቅርበው።
ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና።