ዘኍል 5:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ የገብስ ዱቄት የሆነውን ስለ እርሷ የሚቀርበውን ቁርባን ያምጣ፤ የቅንዓት የእህል ቁርባን ነውና፥ በደልንም የሚያስታውስ የመታሰቢያ የእህል ቁርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፤ የኢፍ መስፈሪያም ዐሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዐት ቍርባን ነውና፥ ኀጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዓት ቍርባን ነውና፥ ኃጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት። Ver Capítulo |