ዘኍል 33:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብጻውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አምስተኛው ቀን ከራዓምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በማግስቱ የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያው ወር ከመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ከግብፃውያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። |
ስለዚህ እያስጨነቁ የግዳጅ ሥራ የሚያሠሯቸውን አሠሪ አለቆች ሾሙባቸው። እስራኤላውያንም ፊቶምና ራምሴ የተባሉ ንብረት ማከማቻ ከተሞችን ለፈርዖን ሠሩለት።