Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 33:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚህ ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር በግብጽ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዚያም ጊዜ ግብፃውያን ጌታ የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ላይ ደግሞ ጌታ ፈረደባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ግብጻውያን በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሞቱትን የበኲር ልጆቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም በአማልክታቸው ላይ እንኳ ፈርዶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 33:4
8 Referencias Cruzadas  

“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።


እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።


እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ በላይ ኀያል እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ፤ እስራኤልን በትዕቢት ይዘው በነበሩት ሁሉ ላይ ይህን አድርጓልና።”


ደግሞም በአገራቸው ያለውን በኵር ሁሉ፣ የኀይላቸውንም ሁሉ በኵራት መታ።


በኵር የሆነ ሁሉ የእኔ ነውና። በግብጽ ምድር በኵር የሆነውን ሁሉ በመታሁ ዕለት ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ማንኛውንም የእስራኤልን በኵር ለራሴ ለይቻለሁ፤ የእኔ ይሁን። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios