Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 47:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብጽ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ፥ ፈርዖን እንዳዘዘም በግብጽ ምድር በተሻለችው የራምሴ ምድር በይዞታ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ በግብጽ ምድር እንዲቀመጡ አደረገ፤ ፈርዖን ባዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ምርጥ የሆነውን፥ በራምሴ ከተማ አጠገብ ያለውን ቦታ በይዞታ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 47:11
13 Referencias Cruzadas  

እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብጻውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”


በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብጽ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፤ በዚያም ሀብት ንብረት ዐፈሩ፤ ቍጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር።


የግብጽ ምድር እንደ ሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኀላፊዎች አድርጋቸው።”


ስለዚህ እያስጨነቁ የግዳጅ ሥራ የሚያሠሯቸውን አሠሪ አለቆች ሾሙባቸው። እስራኤላውያንም ፊቶምና ራምሴ የተባሉ ንብረት ማከማቻ ከተሞችን ለፈርዖን ሠሩለት።


እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ። ከሴቶቹና ከልጆቹ ሌላ፣ ስድስት መቶ ሺሕ እግረኛ ወንዶች ነበሩ።


የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል።


እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብጻውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ።


ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።


እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም።


በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው።


ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን።


ከአንተ ለተቀበላቸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲሰጥ፣ በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥተኸዋልና።


“አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos