በሞዓብ፣ በአሞን፣ በኤዶምና በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩ አይሁድ በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ፣ ሰዎችን በይሁዳ እንዳስቀረና የሳፋን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመ በሰሙ ጊዜ፣
ዘኍል 22:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ ሞዓብ ሜዳ ተጕዘው ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከኢያሪኮ ማዶ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በዮርዳኖስ ማዶ ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ጒዞአቸውን በመቀጠል ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅና በኢያሪኮ ትይዩ በሚገኘው በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢያሪኮ በኩል በዮርዳኖስ አጠገብ በሞዓብ ምዕራብም ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በዮርዳኖስ ማዶ ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። |
በሞዓብ፣ በአሞን፣ በኤዶምና በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩ አይሁድ በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ፣ ሰዎችን በይሁዳ እንዳስቀረና የሳፋን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመ በሰሙ ጊዜ፣
የማረኳቸውን ሰዎች፣ የነዷቸውን እንስሳትና የዘረፉትን ሀብት በሙሉ፣ ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ፣ በሞዓብ ወዳለው፣ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም መላው የእስራኤላውያን ማኅበር ወዳሉበት ሰፈራቸው አመጧቸው።
ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ ሳሉ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዞችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።
ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኘውን፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ ያለውን ግዛት፣ ከእነዚህ ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ላይ ወሰድንባቸው።
ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣
ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።