ፈርዖን በቀረበ ጊዜ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ እነሆ፣ ግብጻውያን ይከታተሏቸው ነበር፤ እነርሱም በታላቅ ፍርሀት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
ዘኍል 20:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛም ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እርሱም ጩኸታችንን ሰምቶ ከግብጽ የሚያወጣንን መልአክ ላከልን፤ እነሆ አሁን እኛ በግዛትህ ወሰን ላይ ባለችው በቃዴስ እንገኛለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። |
ፈርዖን በቀረበ ጊዜ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ እነሆ፣ ግብጻውያን ይከታተሏቸው ነበር፤ እነርሱም በታላቅ ፍርሀት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
ከዚያም ከእስራኤል ሰራዊት ፊት ፊት ሆኖ ሲሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ተመለሰና ወደ ኋላቸው መጣ፤ የደመናውም ዐምድ እንዲሁ ከፊት ተነሥቶ ከኋላቸው ቆመ፤
ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለ ተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ፣ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጐዱኝም።”
“አገርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን፤ ወደ የትኛውም ዕርሻ ሆነ የወይን አትክልት አንገባም፤ ወይም ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስም የንጉሡን አውራ ጐዳና አንለቅም።”
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብጽ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን?
ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል።