እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።
ዘኍል 15:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስእለታችሁን ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማድረግ ወይም በበዓላታችሁ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ከላም ወይም ከበግ መንጋ በእሳት ለእግዚአብሔር ስታቀርቡ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስእለታችሁን ለመፈጸም፥ ወይም በፈቃዳችሁ፥ ወይም በበዓላችሁ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ብታቀርቡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ስለ ስእለት መፈጸም ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በበጎ ፈቃድ ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በተለመዱት የሃይማኖት በዓላት ላይ ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደዚህ ያለውም የምግብ ቊርባን መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፈቃዳችሁም ቢሆን በበዓላችሁም ቢሆን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእለቱን አብዝታችሁ በአመጣችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስእለታችሁን ልትፈጽሙ፥ ወይም በፈቃዳችሁ፥ ወይም በበዓላችሁ፥ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ ታደርጉ ዘንድ ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ብታቀርቡ፥ |
እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።
በዚህም ገንዘብ ወይፈኖችን፣ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን፣ ከእህል ቍርባኖቻቸውና ከመጠጥ ቍርባኖቻቸው ጋራ መግዛት እንዳለብህ አትርሳ፤ እነዚህንም በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላካችሁ ቤተ መቅደስ መሠዊያ ላይ አቅርብ።
ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።
ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ ለእግዚአብሔር መልካም መዐዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ሌላውን የበግ ጠቦት በማለዳው እንደ ቀረበው ተመሳሳይ ከሆነው የእህልና የመጠጥ መሥዋዕት ጋራ በማታ ሠዋው፤ ይህም ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።
ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ።
ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።
ከእነዚህም ጋራ የሚቀርበውን የእህልና የመጠጥ ቍርባን ቂጣ ማለት ከላመ ዱቄት በዘይት የተለወሱ ዕንጐቻዎች እንዲሁም በሥሡ የተጋገረና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ያምጣ።
ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ።
ከዚያም አምላካችሁ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ፣ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፦ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የተሳላችኋቸውን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
የእህልህን፣ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን ዐሥራት ወይም የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት፣ ወይም ለመስጠት የተሳልኸውን ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታህን፣ ወይም የእጅህን ስጦታ፣ በከተሞችህ ውስጥ መብላት የለብህም።
ወደዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ ስእለቶቻችሁንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፣ የቀንድ ከብት መንጋችሁን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አምጡ።
የሚያስፈልገኝን ሁሉ፣ ከሚያስፈልገኝም በላይ ተቀብያለሁ፤ የላካችሁትንም ስጦታ ከአፍሮዲጡ እጅ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ፤ ይህም መዐዛው የጣፈጠ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።