Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 6:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእነዚህም ጋራ የሚቀርበውን የእህልና የመጠጥ ቍርባን ቂጣ ማለት ከላመ ዱቄት በዘይት የተለወሱ ዕንጐቻዎች እንዲሁም በሥሡ የተጋገረና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ያምጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንድ ሌማትም እርሾ ያልገባበት እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ እርሾ ያልገባበት ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቁርባን፥ የመጠጡንም ቁርባን ያቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አንድ ሌማ​ትም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ያቅ​ርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንድ ሌማትም ቂጣ እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን ያቅርብ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 6:15
15 Referencias Cruzadas  

“ ‘በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ የእህል ቍርባን በምታቀርብበት ጊዜ፣ ከላመ ዱቄት ተዘጋጅቶ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ኅብስት ይሁን፤ አለዚያም ያለ እርሾ በሥሡ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ ይሁን።


እርሾ ከሌለው ከምርጥ የስንዴ ዱቄት ቂጣ፣ በዘይት የተለወሰ የቂጣ ዕንጐቻና በዘይት የተቀባ ኅብስት ጋግር።


እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብና ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።


ይህን እንጀራ በምትበሉበት ጊዜ፣ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?


ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።


የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጧል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ ካህናት ያለቅሳሉ።


ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤ የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴ አደባባዮች ይጠጡታል።”


ለኅብረት መሥዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቍርባን ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ”


“አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤


“ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ።


“ ‘ካህኑ እነዚህን የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios