ዘኍል 13:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኔጌብ በኩል ዐልፈው አኪመን፣ ሴሲና ተላሚ የተባሉ የዔናቅ ዝርያዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን መጡ። ኬብሮን የተመሠረተችው ጣኔዎስ በግብጽ ምድር ከመቈርቈሯ ሰባት ዓመት አስቀድሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው ወደ ኔጌብ ሄደው ወደ ኬብሮን መጡ፤ ይህችም ኬብሮን “ዐናቂም” ተብለው የሚጠሩ የግዙፋን ሰዎች ዘር የሆኑ አሒማን፥ ሼሻይ እና ታልማይ የሚባሉት ጐሣዎች መኖሪያ ነበረች። (ኬብሮን የተመሠረተችውም በግብጽ ምድር ጾዓን ተብላ የምትጠራው ከተማ ከመቈርቈርዋ ሰባት ዓመት ቀደም ብሎ ነበር።) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎእ በፊት ሰባት ዓመት ተሠርታ ነበር። |
ከዚህ በኋላ ዳዊት፣ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፣ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት።
ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢብኖብ የተባለ፣ የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ፤ እርሱም ዳዊትን ለመግደል ዐሰበ።
የጣኔዎስ አለቆች በጣም ቂሎች ናቸው፤ የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤ የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ” እንዴት ትሉታላችሁ?
ኔፊሊምንም በዚያ አይተናል፤ የዔናቅ ዝርያዎች የመጡት ከኔፊሊም ነው። ራሳችንን ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።”