Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 21:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እንደዚሁም ለነፍሰ ገዳይ የመማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነመሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰማሪያዋን፥ ልብናንና መሰማሪያዋን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ ከሆነችው ኬብሮን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር በተጨማሪ ለካህኑ ለአሮን ዘሮች ከዚህ የሚከተሉት ከተሞች ተመደቡላቸው፤ እነርሱም ሊብና፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰምርያዋን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 21:13
9 Referencias Cruzadas  

ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው፤ ልብናም በዚሁ ጊዜ ዐምፆ ነበር።


የጦር አዛዡም፣ የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡም ልብናን ሲወጋ አገኘው።


“ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤


ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከመቄዳ ወደ ልብና ዐለፉ፤ ወጓትም።


ልብና፣ ዔቴር፣ ዓሻን


ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያት አርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።


ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።


ይሁን እንጂ በከተማዪቱ ዙሪያ ያሉትን ዕርሻዎችና መንደሮች ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos