ኢያሱ 21:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ለነፍሰ ገዳይ የመማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነመሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰማሪያዋን፥ ልብናንና መሰማሪያዋን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ ከሆነችው ኬብሮን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር በተጨማሪ ለካህኑ ለአሮን ዘሮች ከዚህ የሚከተሉት ከተሞች ተመደቡላቸው፤ እነርሱም ሊብና፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማርያዋን፤ ሌምናንና መሰማርያዋን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰምርያዋን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ |
“ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤
ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።