ኢያሱ 17:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታጱዋ ምድር የምናሴ ይዞታ ነበር፤ ይሁን እንጂ በድንበሩ ላይ የምትገኘው የታጱዋ ከተማ የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታፑሐ ዙሪያ የሚገኘውም ምድር ለምናሴ ተሰጠ፤ በድንበር ላይ የምትገኘው ትንሽዋ የታፑሐ ከተማ ግን የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጣፌት ምድር ለምናሴ ነበረ፤ ጣፌት ግን በኤፍሬም ልጆችና በምናሴ ልጆች አውራጃ ያለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፥ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። |
ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።
የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል።