አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፤ ልጄ ዐውቃለሁ፤ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እንቢ አለው።
ኢያሱ 17:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ልጆች ነገድ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንኩ እስከ አሁንም ጌታ ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ድርሻ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ልጆች ኢያሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስንሆን እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን?” ብለው ወቀሱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን፦ እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንሁ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ክፍል አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ? አሉት። |
አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፤ ልጄ ዐውቃለሁ፤ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እንቢ አለው።
በዚያ ዕለት ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “በአንተ ስም እስራኤል እንዲህ ብሎ ይመርቃል፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ።’ ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።
በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል።
ኢያሱም መልሶ፣ “ቍጥራችሁ ይህን ያህል በዝቶ ኰረብታማው የኤፍሬም ምድር እስከዚህ የሚጠብባችሁ ከሆነ፣ ወደ ፌርዛውያንና ወደ ራፋይም ምድር ወጥታችሁ ደኑን ለራሳችሁ መንጥሩ” አላቸው።