ኢያሱ 15:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገድ ድርሻ በየወገናቸው እስከ ኤዶም ድንበር፥ ወደ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ነገድ ድንበር በየወገናቸው ከኤዶምያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው። |
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋራ በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ።
በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ መሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብጽን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።
ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው።
የሚሠራውን ነገር የሰሙ ሰዎችም ከይሁዳ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከኤዶምያስ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ወደ እርሱ መጡ።
ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፣ በቃዴስ መሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው።