Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 14:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው ሰው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባዕ ነበር፤ ይህም አርባዕ ከዐናቃውያን መካከል ታላቅ ሰው ነበር። ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ የአ​ር​ቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የዔ​ና​ቃ​ው​ያን ዋና ከተማ ነበ​ረች። ምድ​ሪ​ቱም ከው​ጊያ ዐረ​ፈች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያትአርባቅ ትባል ነበር፥ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ከሁሉ ከፍ ያለ ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 14:15
16 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።


በከነዓን ምድር፣ በቂርያት አርባቅ ማለትም በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያለቅስና ሊያዝን መጣ።


የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።


ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ።


ስለዚህ ምድያማውያን በእስራኤላውያን ተሸነፉ፤ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። ጌዴዎን በሕይወት እስካለ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ አርባ ዓመት ሰላም አገኘች።


“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤ አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።” ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።


በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች።


ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይሥሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያት አርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት።


ያዕቆብም፣ “ሄደህ ወንድሞችህም፣ መንጎቹም ደኅና መሆናቸውን አይተህ ወሬያቸውን አምጣልኝ” አለው፤ ከኬብሮንም ሸለቆ ወደ ሴኬም ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣


ስለዚህም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኬብሮን የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ርስት ሆነች፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ተከትሏልና።


እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


ከይሁዳ ሕዝብ ጥቂቱ በመንደሮችና በዕርሻ ቦታዎች፣ በቂርያት አርባቅና በዙሪያዋ ባሉ መኖሪያዎቿ፣ በዲቦንና በመኖሪያዎቿ፣ በይቀብጽኤልና በመንደሮቿ ተቀመጡ፤


ይሁን እንጂ በከተማዪቱ ዙሪያ ያሉትን ዕርሻዎችና መንደሮች ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።


ሙሴ ባዘዘው መሠረት ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ።


በኬብሮን እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በተዘዋወሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከላቸው።


አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios