ዮናስ 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤ አንተም ጩኸቴን ሰማህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ዮናስ ወደ ጌታ ወደ አምላኩ ጸለየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናስም በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ |
በመጣህ ጊዜ ሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣ በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤ በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታት ከዙፋናቸው አውርዳለች።
የጥንት ዘመን ሰዎች ወደ ገቡበት ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ አወርድሻለሁ፤ ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ በጥንቱ ፍርስራሽ ከምድር በታች አኖርሻለሁ፤ ከዚህም በኋላ በሕያዋን ምድር ተመልሰሽ ቦታ አታገኚም፤
ስለዚህ በውሃ አጠገብ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ ጫፎቹን ችምችም ካለው ቅጠል በላይ ከፍ በማድረግ፣ ከእንግዲህ ራሱን በትዕቢት አያንጠራራም። ከእንግዲህ ውሃ በሚገባ ያገኘ ማንኛውም ዛፍ ወደዚህ ዐይነቱ ከፍታ አይደርስም። ሁሉም ከምድር በታች ወደ ጕድጓድ ከሚወርድ ሟች ጋራ ዐብሮ እንዲሞት ተወስኖበታልና።
ዮናስ በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ቈየ፣ እንዲሁ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ ይቈያል።
ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋራ አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።
ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተመራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር በረታ።