ኤርምያስ 7:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እግዚአብሔር ቍጣው የወረደበትን ይህን ትውልድ ስለ ናቀውና ስለ ተወው፣ ጠጕርሽን ቈርጠሽ ጣዪ፤ በባድሞቹ ኰረብቶች ላይ ሆነሽም ሙሾ አውጪ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የቁጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጉርሽን ቁረጪ፥ ጣዪውም፥ በተራቈቱ ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ፥” ትላቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፥ ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ በመጣል እዘኑ፤ ዛፎች በሌሉባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ሙሾ አውጡ፤ እኔ እግዚአብሔር ተቈጥቻለሁ፤ ሕዝቤንም ከፊቴ አሽቀንጥሬ ጥያለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቈርጠሽ፥ ጣዪው፤ በከንፈሮችሽም ሙሾ አውርጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቍረጪ፥ ጣዪውም፥ በወናዎች ኮረብቶችም ላይ አሙሺ። |
ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።
“እስኪ ቀና ብለሽ ጭር ያሉትን ኰረብቶች ተመልከቺ፣ በርኩሰት ያልተጋደምሽበት ቦታ ይገኛልን? በበረሓ እንደ ተቀመጠ ዘላን ዐረብ፣ በየመንገዱ ዳር ተቀምጠሽ ወዳጆችሽን ጠበቅሽ። በዝሙትሽና በክፋትሽ፣ ምድሪቱን አረከስሽ።
ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጥበብን የተሞላህ፣ ፍጹም ውበትን የተላበስህ፣ የፍጹምነት ምሳሌ ነበርህ።
እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የእፉኝት ልጆች! ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ?