Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 48:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል፤ እጅ ሁሉ ተቸፍችፏል፤ ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 “ራስ ሁሉ መላጣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና፤ በእጅም ሁሉ ላይ መተልተል በወገብም ላይ ማቅ አለና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 የሞአብ ሕዝብ በሰገነቶች ላይና በመንገዶች ላይ ሆነው ያለቅሳሉ፤ ወንዶች ጢማቸውን ይቈረጣሉ፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ይላጫሉ፤ እጆቻቸውን ይበጣሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ራስ ሁሉ መላጣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና፥ በእጅም ሁሉ ላይ ክትፋት በወገብም ላይ ማቅ አለና።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:37
22 Referencias Cruzadas  

ሮቤል ወደ ጕድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ።


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤


ስለዚህ እየጮኹ እንደ ልማዳቸው ደማቸው እስኪፈስስ ድረስ ሰውነታቸውን በሰይፍና በጩቤ ያቈስሉ ነበር።


አክዓብም ይህን ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶ፤ ጾመ፤ በማቅ ላይ ተኛ በሐዘን ኵርምት ብሎም ይሄድ ነበር።


ንጉሡም ሴቲቱ ያለችውን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበትም ጊዜ፣ ማቅ ከውስጥ መልበሱን ሕዝቡ አየ።


ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።


በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።


በሽቱ ፈንታ ግማት፣ በሻሽ ፈንታ ገመድ፣ አምሮ በተሠራ ጠጕር ፈንታ ቡሓነት፣ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል።


ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን ሲሰማ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለበሰ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ገባ።


“ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፤ አይለቀስላቸውም፤ ሰውነቱን የሚቧጥጥላቸው፣ ጠጕሩንም የሚላጭላቸው አይገኝም፤


ሰማንያ ሰዎች ጢማቸውን ተላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀድደው፣ ገላቸውን ነጭተው የእህል ቍርባንና ዕጣን በመያዝ ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማቅረብ መጡ።


ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፤ አስቀሎና አፏን ትይዛለች። በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ቅሬታዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?


“ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤ የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋራ፣ ተማርኮ ይወሰዳልና፣ በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።


ስለ አንቺ ጠጕራቸውን ይላጫሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ፤ በነፍስ ምሬት፣ በመራራም ሐዘን ያለቅሱልሻል።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አስቸጋሪ በሆነ ዘመቻ ሰራዊቱን በጢሮስ ላይ አንቀሳቀሰ፤ የሁሉም ራስ ተመልጧል፤ የሁሉም ትከሻ ተልጧል፤ ይሁን እንጂ እርሱና ሰራዊቱ በጢሮስ ላይ ካደረጉት ዘመቻ ያተረፉት ነገር የለም።


ማቅ ይለብሳሉ፤ ሽብርም ይውጣቸዋል። ፊታቸው ኀፍረት ይለብሳል፤ ራሳቸውም ይላጫል።


“ ‘ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ፤ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”


ደስ ለምትሠኙባቸው ልጆቻችሁ፣ በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤ ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤ ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።


በመቃብሮቹና በተራሮቹ መካከል ቀንና ሌሊት እየተዘዋወረ በመጮኽ ሰውነቱን በድንጋይ ይቈራርጥ ነበር።


ለሁለቱ ምስክሮቼ ኀይል እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ማቅ ለብሰው አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ይናገራሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos