ኤርምያስ 48:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በደረቅም መሬት ላይ ተቀመጪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞአብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ፤ በጭቃም ላይ ተቀመጪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዲቦን የምትኖሪ ሆይ፥ ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በጥማትም ተቀመጪ። |
ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብጽ ለምን አወጣኸን?” አሉት።
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
“አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም።
“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”
ይህም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና በሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ እስከ ዲቦን የሚደርሰውን የሜድባን ደጋማ ምድር በሙሉ ይይዛል፤
እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።