Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 13:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሐሴቦንና በደጋው ላይ ያሉትን ከተሞቿን በሙሉ፣ እንዲሁም ዲቦንን፣ ባሞትባኣልን፣ ቤትበኣልምዖን፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሐሴቦንም፥ በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበኣል፥ ቤትባኣልምዖን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንዲሁም ሐሴቦንን፥ በደጋማ አገር ያሉትን ከተሞች፥ ዲቦን፥ ባሞትበዓል፥ ቤትበዓልመዖን፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሐሴቦንም፥ በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞትበኣል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 13:17
17 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ስማቸው የተለወጠውን ናባውን፣ በኣልሜዎንን፣ ሴባማንን ዐደሱ፤ ላደሷቸውም ከተሞች ስም አወጡላቸው።


በማግስቱም ጧት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞትባኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝቡን በከፊል አየ።


ከመቴና ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤልም ወደ ባሞት፣


ድንበራቸው ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና ከሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ ያለው ግዛት ሲሆን፣ ሜድባ አጠገብ ያለውን ደጋውን አገር በሙሉ፣


ያሀጽን፣ ቅዴሞትን፣ ሜፍዓትን፣


ከይሁዳ ሕዝብ ጥቂቱ በመንደሮችና በዕርሻ ቦታዎች፣ በቂርያት አርባቅና በዙሪያዋ ባሉ መኖሪያዎቿ፣ በዲቦንና በመኖሪያዎቿ፣ በይቀብጽኤልና በመንደሮቿ ተቀመጡ፤


በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤ አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ሸለቆው ይጠፋል፤ ዐምባውም ይፈርሳል።


“ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።


በቂርያታይም፣ በቤትጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣


በምድሪቱ ድንበር ላይ ካሉትና ክብሯ ከሆኑት ከተሞች ከቤትየሺሞት፣ ከበኣልሜዎንና ከቂርያታይም ጀምሬ የሞዓብን ዐምባ እገልጣለሁ።


ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።


“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”


ሙሴ ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው፣ የዮርዳኖስን ምሥራቅ ክፍል ርስት አድርጎ ሰጣቸው፤ ሌዋውያኑ ግን ዐብረዋቸው እንዲካፈሉ አላደረገም፤


ሌዋውያኑ ግን ለእግዚአብሔር የሚሰጡት የክህነት አገልግሎት ርስታቸው ስለ ሆነ በእናንተ መካከል ድርሻ አይኖራቸውም። ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምሥራቅ ዮርዳኖስ የሰጣቸውን ርስት ቀደም አድርገው ወስደዋል።”


እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮቿ፣ በአሮዔርና በመንደሮቿ፣ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያ ጊዜ ስለ ምን አልወሰዳችኋቸውም ነበር?


የኢዩኤል ልጅ፣ የሽማዕ ልጅ፣ የዖዛዝ ልጅ ቤላ። እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።


ፍርድ በዐምባው ምድር፦ በሖሎን፣ በያሀጽና በሜፍዓት ላይ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios