ኤርምያስ 13:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ራሱ ልብሳችሁን ገፎ ኀፍረተ ሥጋችሁ እንዲጋለጥ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በስተኋላሽ ወደ ፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። |
“ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ ራስሽን ብትጠይቂ፣ ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣ በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።
እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።
ኢየሩሳሌም ከባድ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህም የረከሰች ሆናለች፤ ያከበሯት ሁሉ ናቋት፤ ዕራቍቷን ሆና አይተዋታልና፤ እርሷ ራሷ ታጕረመርማለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር ብላለች።
በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ።
እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኩሰትሽ፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ፤ ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልበዋለሁ፤ ዕርቃንሽን ለአሕዛብ፣ ኀፍረትሽንም ለነገሥታት አሳያለሁ።