1 ሳሙኤል 13:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን በጌልገላ ቈየ፣ ዐብሮት የነበረውም ሰራዊት ሁሉ በፍርሀት ይንቀጠቀጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕብራውያንም አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፤ አብሮት የተሰለፈው ሠራዊት ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕብራውያን መካከል አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ግዛቶች ሄዱ። ሳኦል ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ በጌልገላ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ከፍርሃት የተነሣ ይንቀጠቀጥ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮርዳኖስንም ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌልጌላ ነበረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርተው እርሱን መከተልን ትተው ተበተኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዕብራውያንም ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ምድር ሄዱ፥ ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበረ፥ ሕዝቡም ሁሉ ተንቀጥቅጠው ተከተሉት። |
እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ።
በዚያ ጊዜ ከያዝነው ምድር ላይ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ በስተሰሜን ያለውን ግዛት፣ በተጨማሪም ኰረብታማውን የገለዓድ አገር እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።
ሌላው የምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ እንደየድርሻቸው ከፋፍሎ በመደበላቸው መሠረት፣ ራሱ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት ተቀበሉ።
‘ማንም የፈራ ቢኖር የገለዓድን ተራራ ትቶ ወደ መጣበት ይመለስ’ ብለህ ለሕዝቡ ዐውጅ።” ስለዚህ ሃያ ሁለቱ ሺሕ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺሕ ብቻ ቀሩ።
በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ሲያዩ፣ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።