ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
ዘካርያስ 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባቸውንም እንደ አለት ድንጋይ አጠነከሩ፤ ጥንት በነበሩት ነቢያት አማካይነት እኔ የሠራዊት አምላክ በመንፈሴ የሰጠኋቸውን ሕግ ሁሉ በእልኸኛነት የማያዳምጡ ሆኑ፤ ስለዚህ እኔ የሠራዊት አምላክ ኀይለኛ ቊጣ አወረድኩባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እጅግ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታም በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ታላቅ ቁጣ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፣ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፥ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ። |
ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።
ስለዚህ እናንተ በጠራኋችሁ ጊዜ መልስ ስላልሰጣችሁና በተናገርኩም ጊዜ ስላላዳመጣችሁ ለእኔ መታዘዝን ትታችሁ ክፉ ማድረግን ስለ መረጣችሁ ዕድል ፈንታችሁ ለገዳይ ተንበርክኮ በሰይፍ መገደል ይሆናል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ኃጢአታችሁ በብረት ብዕር ተጽፎአል፤ ሹል በሆነው አልማዝ በልባችሁ ጽላትና በመሠዊያዎቻችሁ ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል።
ታዲያ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሚክያስ እንዲገደል አደረጉን? አይደለም! ይልቁንም ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በመፍራት ምሕረት እንዲያደርግለት ተማጠነ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ዐቅዶት የነበረውን መቅሠፍት መለሰ፤ እኛ ግን አሁን አሠቃቂ የሆነ መቅሠፍት በራሳችን ላይ ለማምጣት ተዘጋጅተናል።”
እነሆ ዛሬ እኔም መልሱን ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድነግራችሁ በእኔ አማካይነት ለላከላችሁ ቃል ሁሉ ታዛዦች አልሆናችሁም።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ስለዚህ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሴ በተሠራበት በዚህ ቦታ ላይ ብርቱ ቊጣዬን አፈሳለሁ፤ በሰዎችና በእንስሶች ላይ፥ በዛፎችና በሰብልም ሁሉ ላይ ሳይቀር አፈሰዋለሁ፤ ቊጣዬ ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል እሳት ይሆናል።
አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ አዲስ መንፈስንም በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ከሰውነታቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣቸዋለሁ።
አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘካርያስን ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ተናገር አለው፦ “እኔ እግዚአብሔር በቀድሞ አባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቼ ነበር፤
ኢየሩሳሌም በልጽጋና በሕዝብ ተሞልታ በነበረችበት ጊዜ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ባሉ መንደሮች ብቻ ሳይሆን በደቡብ ክፍልና በምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ ብዙ ሕዝብ በሚኖሩበት ዘመን እግዚአብሔር በቀድሞ ነቢያቱ አማካይነት የተናገረውም ይህንኑ ቃል ነበር።
የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’
ይህም የሚሆነው፥ ‘እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ኃጢአታቸው ይቅር እንዳይባልላቸው፥ ማየትን እያዩ ልብ አያደርጉም፤ መስማትን እየሰሙ አያስተውሉም፤’ ” በተባለው መሠረት ነው።
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።
የእነዚህ ሰዎች ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ተጨፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተዘግቶአል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና እኔም በፈወስኩአቸው ነበር።’