ዘካርያስ 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ የይሁዳን ሕዝብ አለቆች በእሳት ማንደጃ ላይ ተከምሮ እንደሚነድ እንጨት፥ በእህል ነዶዎች መካከል እንደ ተቀጣጠለ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ በአካባቢው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያወድማሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን ምንም ሳይደርስባቸው በከተማይቱ ውስጥ ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በዕንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ፣ በነዶም መካከል እንዳለ የፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በግራና በቀኝ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌም ግን ከስፍራዋ ንቅንቅ አትልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በቀኝና በግራ በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፤ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ ትኖራለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፥ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፥ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች። |
በአንድ በኩል ሆዳቸው እስኪሞላ ይበላሉ፤ ነገር ግን እንደ ተራቡ ናቸው፤ እንዲሁም በሌላ በኩል አግበስብሰው ይውጣሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ የልጆቻቸውን ሥጋ እንኳ እስከ መብላት ይደርሳሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።
የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥ የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥ የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ። ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”
በዚያን ጊዜ የይሁዳ አለቆች በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆነ በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሕዝቡ በእርሱ ኀይልን ያገኛሉ’ ይላሉ።
የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይከላከልላቸዋል፤ እነርሱም ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ የጠላትንም የወንጭፍ ድንጋይ ይረጋግጣሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የጠላቶቻቸውም ደም የመሥዋዕት ደም በሳሕን ሞልቶ በመሠዊያ ላይ እንደሚፈስስ ይፈስሳል።